ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝደንት ለመምረጥ በ19/12/2014 ዓ.ም በወጣው የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ መሠረት ከተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛውን መስፈርት በማሟላት የቀረቡ ተወዳዳሪዎች በመመሪያው መሠረት የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት እና ነባር መምህራን ወይም ተመራማሪዎች በተገኙበት የስትራቴጅክ ዕቅድ ገለጻ የሚደረግ ስለሆነ የኢንስቲትዩቶች፣ የኮሌጆች እና የት/ቤቶች ዲኖችና ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች እንዲሁም የአስተዳደር ዳይሬክተሮች ከየዘርፋችሁ የካውንስል አባላት እና ከየትምህርት ክፍሉ አንድ አንድ ነባር/Senior/ መምህር ወይም ተመራማሪ ይዛችሁ በ5/03/2015 ዓ.ም 2፡3ዐ በዋናው ግቢ መግቢያ በር አካባቢ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. የኢንስቲትዩት፣ የኮሌጆች እና የት/ቤት ኃላፊዎችና የአስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክተሮች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የካውንስል አባላትን ብቻ በመያዝ በሰዓቱ እንድትገኙ፤
  2. የካውንስል አባላት በተወካዮቻቸው አማካይኝነት መሳተፍ እንደማይችሉ በማሳወቅ ራሳቸው እንዲገኙ ጥብቅ መልዕክት እንዲተላለፍ፤
  3. የካውንስል አባላት በሰዓቱ በመገኘት የሁሉንም ስትራቴጂክ ገለፃዎች የመከታተል ግዴታ እንዳለባቸው እንዲያውቁ እንዲደረግ፡፡

 የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት