በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሒሳብ ትምህርት ከፍል በ‹‹Opበአርባ ምንጭ ዩኒቨርeration Research›› ትምህርት ፕሮግራም  የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ ፀጋዬ የምርምር ሥራቸውን ኅዳር 3/2015 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርበው ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ እና የ2ኛ ዲግሪያቸውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማግኘት በአክሱም እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው የ3ኛ ዲግሪ ትህርታቸውን በ 2009ዓ/ም አጋማሽ ላይ የጀመሩት ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ መመረቂያ ጽሑፋቸውን በ‹‹Application of Intuitionistic Fuzzy Optimization Technique in the Determination of Optimal Cropping Pattern›› በሚል ርዕስ ላይ አከናውነዋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኙ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የዘርፉ መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡                                                                                                                                                                                                      

                                                                                                                                                                                                                           የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት