አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ላለፉት ዓመታት በፕሬዝደንትነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የመጀመሪያ ዙር የሹመት ዘመን መጠናቀቅን ተከትሎ 13 ተፎካካሪዎች የተሳተፉበት ይፋዊ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተካሂዶ በድጋሚ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ሆነው ተሹመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር ታኅሣሥ 06/2015 ዓ/ም በቁጥር 1/158/898/15 በጻፈው የሹመት ደብዳቤ በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርም ዕቅድ መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ መልሶ እስኪደራጅና አዲስ ፕሬዝደንት በዓለም አቀፍ ውድድር እስኪቀጠር ድረስ ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ  ከታኅሣሥ 15/2015 ዓ/ም ጀምሮ በድጋሚ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ሆነው መሾማቸውን በመግለጽ ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮውን ያሳካ ዘንድ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት በትጋት እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እጅግ ፈታኝ በሆነው ጊዜ ውስጥ የዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ከፌዴራልና ከአካባቢው መንግሥት ጋር በቅንጅት በመሥራት ማስቀጠል መቻላቸው ይታወሳል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት