አርባ  ምንጭ ዩኒቨርሲቲን  ለ2ኛ ዙር በፕሬዝደንትነት ለማገልገል በመሾሜ ከፍ ያለ ደስታ የተሰማኝ መሆኑን በታላቅ አከብሮት እየገለጽኩኝ ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢውና ለሀገራችን ዕድገት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተልዕኮዎች አኳያ  የሚጠበቅበትን በላቀ ደረጃ እንዲያበረክት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ደረጃና ዝና ከፍ ለማድረግ ሁላችንም ተቀናጅተንና ተባብረን እንሥራ፡፡

በ2ው ዙር የሥራ ዘመኔ ከመጀመሪያው ዙር በተሻለ ደረጃ ዩኒቨርሲቲውን ለማገልገል የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ ቀጣዩ ዘመን ለሀገራችንና ለሕዝባችን ሙሉ የሠላምና የብልጽግና እንዲሆን እመኛለሁ!

ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር)