በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ በ“Geography and Environmental Studies” ትምህርት ክፍል በ“Disaster Risk Management” ትምህርት ፕሮግራም ላላፉት 5 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር መኩሪያ ጉዬ የምርምር ሥራውን ሰኔ 24/2015 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቦ ተገምግሟል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር መኩሪያ የመመረቂያ ጽሑፉን “LIVING WITH DROUGHT: VULNERABILITY, IMPACTS AND PASTORALISTS’ QUEST OF RESILIENCE AT BURKITU WATERSHED IN DUGDA DAWA DISTRICT, SOUTHERN ETHIOPIA” በሚል ርዕስ ያከናወነ ሲሆን የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

ዕጩ ዶ/ር መኩሪያ ጉዬ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ“Geography and Environmental Studies” እና 2ኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ትምህርት መስክ ያገኘ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቷል፡፡

በግምገማ መርሃ ግብሩ ፕ/ር ደገፋ ቶሎሳ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ዶ/ር መንበሩ ተሾመ ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በውጭ ገሚጋሚነት እንዲሁም ዶ/ር የቻለ ከበደ በውስጥ ገምጋሚነት የተሳተፉ ሲሆን የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የዘርፉ መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር መኩሪያ ጉዬ የዶክትሬት ዲግሪውን በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት