አርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ2015 ዓ/ም ዕጩ ተመራቂ የኮሚዩኒኬሽንና ኮምፒውተር ምኅንድስና ተማሪዎች እንዲሁም ለኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምኅንድስና መምህራን ‹‹5G and 3GPP Radio Access Network and Evolution of 3Gpp Based Radio Access Network (RAN) for Mobile Communication›› በሚል ርእስ ሰኔ 29/2015 ዓ/ም ትምህርታዊ ሴሚናር አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በስዊድኑ ‹‹Ericsson›› ካምፓኒ ስትራቴጂክ ፕሮዳክት ማኔጀር የሆኑትና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ባልደረባ አቶ ብሩክ ሥላስ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሴሉላር ሞባይል ኔትዎርከ ከ‹‹1G›› ተነስቶ እስከ ‹‹5G›› እንዴት እየተሻሻለና እያደገ እንደመጣ፣ በአጠቃላይ ሞባይል ኮሚዩኒኬሽን ላይ የሚገጥሙ ችግሮችና የሚፈቱበት ዘዴ ላይ ገለጻና ማሳያ አቅርበዋል፡፡ ሴሚናሩ ወደ ፊት በቴክኖሎጂ ዙሪያ ምን ዓይነት ምርምሮች መሠራት እንዳለባቸው ለተሳታፊዎቹ ግንዛቤ እንደሚፈጥር አቶ ብሩክ ተናግረዋል፡፡

የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምኅንድስና ፋከልቲ ዲን አቶ ሳተናው ሳንዶ እንደገለጹት በመማር ማስተማር ሂደት ተግባር ተኮር ሥልጠና ላይ ትኩረት ማድረግ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ ሲሆን በተለይም በኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ባለሙያዎች ልምዳቸውን ሲያካፍሉ የተማሪዎችንና የመምህራን ዕውቀት ከፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

5ኛ ዓመት የኤሌክትሪካል ምኅንድስና ተማሪ ቢንያም ልዑልሰገድና የኮሚዩኒኬሽንና ኮምፒውተር ምኅንድስና ተማሪ በረከት ጩፋሞ በሰጡት አስተያየት ከሴሚናሩ ዓለም በቴክኖሎጂ የደረሰችበትን ደረጃ እንዲሁም የኮሚዩኒኬሽን ሥርዓት ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ግንዛቤ ያገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት