አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበው የመጡ የመጀመሪያ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ፈታኞች፣ የፈተና አስፈጻሚዎችና አስተባባሪዎች ቅበላና አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ ገለጻ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በስድስቱም ካምፓሶቹ 11,773 ወንድ እና 12,354 ሴት በድምሩ 24,127 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር መርሃ ግብር መሠረት ፈተናውን ከሐምሌ 19/2015 ዓ/ም ጀምሮ የሚወስዱ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

 

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት