አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ “SNV-Rayee” ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚገኙ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ያዘጋጀ በመሆኑ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በውድድሩ ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. የውድድሩ መስፈርት
  • ዕድሜ፡ ከ18-35 ዓመት
  • ጾታ፡ አይለይም
  • አመልካቾች በአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ መሆንና የቀበሌ ድጋፍ ወይም የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከአርባ ምንጭ ከተማ ውጭ ለሆኑ ነዋሪዎች ውድድሩ አይመለከታቸውም
  • ሥራ አጥ ወጣቶች፣ የንግድ ሥራ የጀመሩ እንዲሁም በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ መወዳደር ይችላሉ
  • በአነስተኛና ጥቃቅን የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ከሆኑ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
  • አመልካቾች የሚወዳደሩበት የንግድ ሃሳብ ከዚህ በፊት በየትኛውም ዓይነት ንግድ ሃሳብ ውድድር ተወዳድረው ያልተሸለሙ መሆን አለባቸው
  • ወጣት ሴት ሥራ ፈጣሪዎች እና አካል ጉዳተኛ ወጣቶች ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል
  • ወጣቶች በሚወዳደሩበት አዲስ የፈጠራ ሃሳባቸው ላይ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
  1. የንግድ ሃሳብ ውድድር ዘርፎች
  • በግብርና ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ሂደቶችን ያማከለ፣ ማምረት እና አቅርቦትን ጨምሮ አሁን ያለውን የምርት፣ የግብይት እና የማቀነባበር ችግሮች ለመቅረፍ የሚረዳ
  • በተመረጡ የዕሴት ሠንሰለቶች (የዶሮ እርባታ፣ የእንስሳት ማድለብ፣ የወተት ምርት፣ አትክልት እና ማር)
  • ጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳት እና አነስተኛ የእጅ ሥራዎች
  • የቀርከሃ እና የቆዳ ሥራ ዘርፎችን ጨምሮ ማንኛውም ዕሴት የሚጨምሩ ተግባራት
  1. ሽልማት

1 ለወጡ 100,000 ብር

2 ለወጡ 80,000 ብር

3 ለወጡ 60,000 ብር

  1. የምዝገባ ቦታ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ጸጥታና ደኅንነት ቢሮ አጠገብ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል ጽ/ቤት

  1. ለበለጠ መረጃ፡-
    • ኢሜል፡ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
    • ስልክ፡

0910451411 ወይም

0996847492

  1. ምዝገባ የሚያልቅበት ቀን:- መስከረም 04/2016 ዓ/ም

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

 

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት