አቶ ታምራት ኃይሌ ከአባታቸው ከአቶ ኃይሌ ገበየሁ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወላንሳ ተፈራ በቀድሞው ወሎ ክፍለ ሀገር ተንታ አካባቢ ሚያዝያ 10/1980 ዓ.ም ተወለዱ፡፡

አቶ ታምራት የ1ና የ2ደረጃ ትምህርታቸውን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፓዊ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ አቶ ታምራት በአፕላይድ ማቲማቲክስ/Applied Mathematics/ ትምህርት መስክ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 8/2002 ዓ/ም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው በሲቭል ምኅንድስና የትምህርት መስክም ከ2006 ዓ/ም - 2010 ዓ/ም ትምህርታቸውን ተከታትለው ሰኔ 20/2010 ዓ/ም  በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

አቶ ታምራት ከመስከረም 1/2003 ዓ/ም- ኅዳር 30/2005 ዓ/ም የተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ፕሮግራም  በኮንትራት፣ ከታኅሣሥ 1/2005 ዓ/ም - ታኅሣሥ 30/2006 ዓ/ም በተማሪዎች አገልግሎት ማዕከል ዳይሬክቶሬት የሪከርድ ፕሮሰሲንግና አካዳሚክ ክሪደንሺያል ባለሙያ 111 በቋሚ ቅጥር፣ ከጥር 01/2006 ዓ/ም - ታኅሣሥ 30/2010 ዓ/ም በቤተመጻሕፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት መለስተኛ የቤተመጻሕፍት ኤሌክትሮኒክስ ሪሶርስ አገልግሎት ባለሙያ፣ ከጥር 01/2010 ዓ/ም - መጋቢት 30/2011 ዓ/ም በተቋማዊ ጥራት ማጎልበቻ ዳይሬክቶሬት የመረጃ አያያዝ ባለሙያ 111፣ ከመስከረም 01/2011 ዓ/ም - ሰኔ 30/2011 ዓ/ም በዋና ሬጂስትራር ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ባለሙያ III፣ ከሐምሌ 01/2011 ዓ/ም - ሰኔ 30/2013 በተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት የመረጃ ሥራ ባለሙያ III እንዲሁም ከሐምሌ 2013 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ነሐሴ 18/2015 ዓ/ም ድረስ በሬጂስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራር II በመሆን ዩኒቨርሲቲውን በቅንነት፣ ታማኝነትና ትጋት አገልግለዋል፡፡

አቶ ታምራት ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ነሐሴ 18/2015 ዓ/ም በ35 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ታምራት ገበየሁ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት