የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ባች 1ኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች፣ የ2014 ባች 2ኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እና የ2012 ባች 4ኛ ዓመት የህግ ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ቅበላ፣ ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበት ቀን እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፡፡

1ኛ.  የቅበላ ቀን፦ እሁድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም፣

2ኛ.  የምዝገባ ቀን፦ ሰኞ እና ማክሰኞ መስከረም 21 እና 22 ቀን 2016 ዓ.ም፣

3ኛ.  በቅጣት የምዝገባ ቀን፦ ረቡዕ መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ብቻ እና

4ኛ.  ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፡- ረቡዕ መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም

መሆኑን በአጽንዖት እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማይቀበል እንዲሁም ምዝገባ የሚፈፀመው በአካል በመገኘት መሆኑን ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ፡-

የ2012 ባች 5ኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ምኅንድስና ተማሪዎች እና የሁሉም ፕሮግራሞች የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቅርቡ የሚገለጽ መሆኑን እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት በመከታተል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች መግቢያ ወደ ፊት ከትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጥ አቅጣጫ መሠረት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት