በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በእንስሳት ሳይንስ ትምህርት ክፍል በእንስሳት ሥነ-ምግብ/Animal Nutrition/ ትምህርት ፕሮግራም የ3ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ከበደ ገልገሎ የምርምር ሥራውን መስከረም 15/2016 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት አቅርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ከበደ የመጀመሪያ ዲግሪውን በ2002 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና የ2 ዲግሪውን በ2006 ዓ.ም ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ  አግኝቷል፡፡ በመምህርነት ሲያገለግል ቆይቶ የ3 ዲግሪ ትምህርቱን በ2010 ዓ/ም የጀመረው ዕጩ ዶ/ር ከበደ ገልገሎ የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሑፉን “Livestock Feed Potentials of Commelina Species In Konso Zone, Southern Ethiopia: Principles and Practices” በሚል ርዕስ አከናውኗል፡፡

ዕጩ ዶ/ር ከበደ የዶክትሬት ዲግሪውን በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኝ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ በውጪ ገምጋሚነት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕ/ር አዱኛ ቶሌራ፣ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕ/ር ታዬ ቶለማርያም እና በውስጥ ገምጋሚነት ዶ/ር አሸናፊ አዛገ እንዲሁም የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ፣ የዘርፉ መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት