የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ባች 5 ዓመት ቅድመ ምረቃ ምኅንድስና ተማሪዎች እና የመደበኛ፣ የማታ እና የሳምንት መጨረሻ የድኅረ ምረቃ (ማስተርስ እና ፒ.ኤች.ዲ) 2 ዓመት 1 ሴምስቴርና ከዚያ በላይ ተማሪዎች ቅበላ፣ ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበት ቀን እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፡፡

1ኛ.  የቅበላ ቀን፦ ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2016 ዓ.ም፣

2ኛ.  የምዝገባ ቀን፦ ሐሙስ እና ዓርብ ጥቅምት 8 እና 9 ቀን 2016 ዓ.ም፣

3ኛ.  በቅጣት የምዝገባ ቀን፦ ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ብቻ እና

4ኛ.  ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፡- ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

መሆኑን በአጽንዖት እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማይቀበል እንዲሁም ምዝገባ የሚፈፀመው በየካምፓሶቻችሁ በአካል በመገኘት መሆኑን ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ፡- የ2016 ባች 1 ዓመት የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን የ“GAT” ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እንደታወቀ በቅርቡ የሚገለጽ መሆኑን እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) በመከታተል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች መግቢያ ከትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጥ አቅጣጫ መሠረት በቅርብ ቀን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት