በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ2016 ትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና /National Graduate Admission Test – NGAT/ ያለፋችሁ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ ማታ እና ሳምንት መጨረሻ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር የምትፈልጉ አመልካቾች ከሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ዓርብ ጥቅምት 23/2016 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 210 እና 211 ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

1ኛ. ለምዝገባ መምጣት ያለባቸው አመልካቾች አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50%) እና በላይ ጥያቄዎች የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል ያገኙ ተፈታኞች ብቻ ይሆናሉ፡፡

2ኛ. አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ የ“NGAT” ፈተና ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ ይጠበቃል፡፡

3ኛ. የማስተርስ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም የፒ.ኤች.ዲ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ኦፍሻል ትራንስክሪፕት በፖስታ ሳጥን ቁጥር 21 ወይም በተቋማዊ ኢሜይል አድራሻዎች This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
      ወይም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. በኩል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት