አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከክርስቲያን ኤይድ/Christian Aid/ ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን ካምባ ዙሪያ ወረዳ ዲንጋሞ ቀበሌ በማይጸሌ ወንዝ ላይ እያስገነባ ለሚገኘው ፒኮ ሃይድሮፓወር ፕሮጀክት የሚውሉና ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ተርባይን፣ ጄኔሬተርና የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ ከሕንድ ሀገር ጥቅምት 22/2016 ዓ/ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

15 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የዲንጋሞ ፒኮ ሃይድሮፓወር ፕሮጀክት እስከ አሁን 85 በመቶው የተጠናቀቀ ሲሆን ከላይ የተገለጹት የፕሮጀክቱ ወሳኝ ግብዓቶች መድረስ ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የጎላ ሚና ይኖረዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ ቡድን አባላት፣ ለዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ሥራ ክፍሎች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ሥራ ላዩ ያሉና የቀድሞ ሠራተኛ የነበሩ የሕንድ መምህራን በግብዓቶቹ ግዥ ሂደት ላይ ላበረከቱት ልዩ አስተዋጽዖ ምሥጋና ተችሯቸዋል፡፡ 

በዩኒቨርሲቲው የተከናወነ የምርምር ሥራን መሠረት በማድረግ እየተሠራ የሚገኘው ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከ600 በላይ የዲንጋሞ ቀበሌ አባወራዎችን የ24 ሰዓት የመብራት ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት