የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤት በስሩ ከሚገኙ ኢንስቲትዩቶች፣ ኮሌጆች፣ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር የ2016 ዓ/ም ዕቅድ የውል ስምምነት ጥቅምት 26/2016 ዓ/ም ተፈራርሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ ያለ ዕቅድ መሥራት በጨለማ እንደመጓዝ በመሆኑ ከስምምነቱ በኋላ ዕቅድን ወደ ታችኛው የሥራ ክፍል በማውረድ የተሻለ አፈፃፃም ለማስመዝገብ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ልዩ ረዳት ዶ/ር ነጅብ መሐመድ በበኩላቸው የዕቅድ ስምምነት መርሃ ግብሩ በቀጣይ በየዘርፉ ሊከናወኑ በሚገቡ ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስንና ሥራዎች በዕቅድ ላይ ተመሥርተው እንዲከናወኑ ማስቻልን ዓላማ በማድረግ  የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት