የትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ዙር ኅዳር 5 እና 6 ቀን 2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በበይነ መረብ ይሰጣል፡፡ ይህ የመግቢያ ፈተና በ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በማንኛውም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድኅረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ የሆኑ አመልካቾችን ለመለየት አልሞ የሚሰጥ ሲሆን አዲስና ፈተናውን ደግመው የሚወስዱ አመልካቾች እስከ ኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ምሽቱ 12፡00/አሥራ ሁለት ሰዓት/ ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖርታልን (https://portal.aau.edu.et) ተጠቅመውና በቴሌብር 1000.00 ብር ከፍለው መመዝገብ ይችላሉ፡፡

የመግቢያ ፈተናውን በተመለከተ አመልካቾች የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድረ ገጽን እና ቴሌግራም ቻናሎች (https://t.me/aauGAT and AAU-Official) ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን መጎብኘት ይችላሉ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት