የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2016 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ ክንውን ሪፖርት ጥቅምት 27/2016 ዓ/ም ቀርቦ ገምግሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት አቅጣጫዎችና ስትራቴጂካዊ ግቦች አንጻር የቀረበውን የሩብ ዓመት ሪፖርት በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ደካማ አፈጻጸም የታየባቸው መስኮችን በመለየት በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት ሰጥቶ ለመሥራት የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር መርሃ ግብሩ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት፣ ትግበራና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰሎሞን ይፍሩ ባቀረቡት ሪፖርት እንደተመለከተው የ12 ሥርዓተ ትምህርቶች ክለሳ ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ፣ ለሁለት መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት፣ ለ14 መምህራን የረዳት ፕሮፌሰርነት፣ ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመለሱ ዘጠኝ መምህራን የሌክቸረርነት አካዳሚክ መዕረግ እንዲያገኙ መደረጉ፣ መምህራን በሚያስተምሩት ዐቢይ ትምህርት የበቁ እንዲሆኑ በሀገር ውስጥ ሦስት የ3 ዲግሪ፣ በውጭ ሀገር አንድ የ2 ዲግሪ እና 10 የ3 ዲግሪ የትምህርት ዕድል መስጠት መቻሉ በአካዳሚክ ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

በሩብ ዓመቱ 13 ነባር ምርምሮች መጠናቀቃቸው፣ የ9.88 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ከትብብር ፕሮጀክቶች መገኘቱ፣ ለ2,070 የማኅበረሰብ ክፍሎች ነፃ የሕግ ጥብቅና፣ የምክር አገልግሎትና የሠነድ ዝግጅት ድጋፍ መሰጠቱ፣ በ “STEM” ማዕከል ከሰባት ዞኖች በመስፈርቱ መሠረት ለተወጣጡ 175 2 ደረጃ ት/ቤቶች ሥልጠና መሰጠቱ፣ የተለያዩ የአካባቢና ደን ጥበቃ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ እና የእንሰት ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋትና ለማስተዋወቅ በ“USAID” ከሚደገፍ ‹‹የኢትዮጵያ ትራንስፎርሚንግ አግሪካልቸር›› የተሰኘ ድርጅትና ቴክኖሎጂዎቹን ከሚያመርቱ አምስት የግል ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመሥራት የሦስትዮሽ መግበቢያ ሠነድ መፈረሙ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ፈጣራና ሽግግር እና በማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፍ በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ለዩኒቨርሲቲው 113 አዳዲስና ነባር ተሽከርካሪዎች ሙሉ የኢንሹራንስ አገልግሎት ግዢ መፈጸሙ፣ የ1,200 ካሬ የመልክዓ ምድር (Land Scape) ሥራ መከናወኑ፣ 9,433,129.90 ብር ከውስጥ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ፣ ለዩኒቨርሲቲው የመማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ተማሪዎችና ስፔሻሊስት ሐኪሞች መኖሪያ የሚሠራበትን ቦታ ድንበር ማስወሰንና ለ26 ተነሺ አባወራዎች የካሳ ክፍያ ተፈጽሞ ነዋሪዎችን ከቦታው የማስለቀቅ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ እንዲሁም ለሥራ ተቋራጮች የዋጋ ማካካሻ እንዲከፈላቸው በተወሰነው መሠረት ክፍያ እየተፈጸመ መሆኑ በአስተዳደርና ልማት ዘርፍ በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

የተማሪ ምግብ ጥሬ ዕቃን ጨምሮ የግብዓት አቅርቦት የገበያ ዋጋ ንረት፣ የግንባታ ሥራ ተቋራጮች የዋጋ ጭማሪ ለውጥ/escalation/ በመጠባበቅ የግንባታዎች ክንውንን ማቀዛቀዝ፣ ከውጭ የሚገዙ የትምህርትና የግንባታ ግብዓቶች ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ አቅራቢዎች በውል በተቀመጠ ጊዜ መሠረት መፈጸም አለመቻል፣  በዩኒቨርሲቲው ዓመታዊ በጀት መሠረት በየወሩ ከገንዘብ ሚኒስቴር ከሚለቀቀው የገንዘብ መጠን ጋር ባለመጣጣምና በገበያ ዋጋ መናር ምክንያት የምርምርና ሌሎች የልማት ሥራዎችን በታቀደው ልክ መፈጸም አለመቻል በሩብ ዓመቱ ካጋጠሙ ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡

የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የአስተዳደር ዘርፍ ሥራዎችን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የመሥራት ደረጃን ለማሻሻል በትኩረት መሥራት፣ የምርምር ሥራ ውጤቶችና የተላመዱና የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ የማሸጋገር ሥራ አጠናክሮ መሥራት፣ ከኦዲት ግኝት የጸዳ ተቋም ለመሆን በትኩረት መሥራት፣ የገቢ ማመንጫ አማራጮችን በማበራከትና አሠራሮችን በማሻሻል ገቢን ማሳደግ፣ ነባር የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና አዲስ የተጀመሩት በብቃት እንዲሠሩ ትኩረት ሰጥቶ መደገፍ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሠረት የሠራተኛ ምደባ ሥራን በትኩረት ማከናወን በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም ‹‹Ethiopian Higher Education, Leadership, Management and Governance Training for Public Higher Education Institution Leaders /LMG/›› በሚል ርእስ በተሰጠው የ10 ቀናት ሥልጠና እና አሜሪካ ሀገር በሚገኙ በቴክሳስ/Texas/፣ ኦክላሆማ/Oklahoma/ እና ኦህዮ/Ohio/ ዩኒቨርሲቲዎች የልምድ ልውውጥ ላይ የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን በቆይታቸው ከተቋማቱ አደረጃጀት፣ ከመምህራን ደመወዝ አከፋፈል፣ ከስፖርትና መዝናኛ መሠረት ልማቶች አሠራርና አጠቃቀም፣ ከበጀት ምንጭ፣ ከምድረ ግቢ ውበት፣ ከቀድሞ ምሩቃን አደረጃጀትና ሚና፣ ከኮሚዩኒኬሽንና ብራንዲንግ አንጻር የተመለከቷቸውን አዳዲስ ልምዶችንና አሠራሮችን የተመለከተ ገለጻ ለካውንስሉ በማቅረብ ልምድ አጋርተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የዩኒቨርሲቲው የ2016 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ተገመገመ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2016 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ ክንውን ሪፖርት ጥቅምት 27/2016 ዓ/ም ቀርቦ ገምግሟል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት አቅጣጫዎችና ስትራቴጂካዊ ግቦች አንጻር የቀረበውን የሩብ ዓመት ሪፖርት በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ደካማ አፈጻጸም የታየባቸው መስኮችን በመለየት በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት ሰጥቶ ለመሥራት የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር መርሃ ግብሩ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት፣ ትግበራና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰሎሞን ይፍሩ ባቀረቡት ሪፖርት እንደተመለከተው የ12 ሥርዓተ ትምህርቶች ክለሳ ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ፣ ለሁለት መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት፣ ለ14 መምህራን የረዳት ፕሮፌሰርነት፣ ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመለሱ ዘጠኝ መምህራን የሌክቸረርነት አካዳሚክ መዕረግ እንዲያገኙ መደረጉ፣ መምህራን በሚያስተምሩት ዐቢይ ትምህርት የበቁ እንዲሆኑ በሀገር ውስጥ ሦስት የ3 ዲግሪ፣ በውጭ ሀገር አንድ የ2 ዲግሪ እና 10 የ3 ዲግሪ የትምህርት ዕድል መስጠት መቻሉ በአካዳሚክ ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

በሩብ ዓመቱ 13 ነባር ምርምሮች መጠናቀቃቸው፣ የ9.88 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ከትብብር ፕሮጀክቶች መገኘቱ፣ ለ2,070 የማኅበረሰብ ክፍሎች ነፃ የሕግ ጥብቅና፣ የምክር አገልግሎትና የሠነድ ዝግጅት ድጋፍ መሰጠቱ፣ በ “STEM” ማዕከል ከሰባት ዞኖች በመስፈርቱ መሠረት ለተወጣጡ 175 2 ደረጃ ት/ቤቶች ሥልጠና መሰጠቱ፣ የተለያዩ የአካባቢና ደን ጥበቃ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ እና የእንሰት ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋትና ለማስተዋወቅ በ“USAID” ከሚደገፍ ‹‹የኢትዮጵያ ትራንስፎርሚንግ አግሪካልቸር›› የተሰኘ ድርጅትና ቴክኖሎጂዎቹን ከሚያመርቱ አምስት የግል ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመሥራት የሦስትዮሽ መግበቢያ ሠነድ መፈረሙ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ፈጣራና ሽግግር እና በማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፍ በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ለዩኒቨርሲቲው 113 አዳዲስና ነባር ተሽከርካሪዎች ሙሉ የኢንሹራንስ አገልግሎት ግዢ መፈጸሙ፣ የ1,200 ካሬ የመልክዓ ምድር (Land Scape) ሥራ መከናወኑ፣ 9,433,129.90 ብር ከውስጥ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ፣ ለዩኒቨርሲቲው የመማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ተማሪዎችና ስፔሻሊስት ሐኪሞች መኖሪያ የሚሠራበትን ቦታ ድንበር ማስወሰንና ለ26 ተነሺ አባወራዎች የካሳ ክፍያ ተፈጽሞ ነዋሪዎችን ከቦታው የማስለቀቅ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ እንዲሁም ለሥራ ተቋራጮች የዋጋ ማካካሻ እንዲከፈላቸው በተወሰነው መሠረት ክፍያ እየተፈጸመ መሆኑ በአስተዳደርና ልማት ዘርፍ በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

የተማሪ ምግብ ጥሬ ዕቃን ጨምሮ የግብዓት አቅርቦት የገበያ ዋጋ ንረት፣ የግንባታ ሥራ ተቋራጮች የዋጋ ጭማሪ ለውጥ/escalation/ በመጠባበቅ የግንባታዎች ክንውንን ማቀዛቀዝ፣ ከውጭ የሚገዙ የትምህርትና የግንባታ ግብዓቶች ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ አቅራቢዎች በውል በተቀመጠ ጊዜ መሠረት መፈጸም አለመቻል፣  በዩኒቨርሲቲው ዓመታዊ በጀት መሠረት በየወሩ ከገንዘብ ሚኒስቴር ከሚለቀቀው የገንዘብ መጠን ጋር ባለመጣጣምና በገበያ ዋጋ መናር ምክንያት የምርምርና ሌሎች የልማት ሥራዎችን በታቀደው ልክ መፈጸም አለመቻል በሩብ ዓመቱ ካጋጠሙ ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡

የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የአስተዳደር ዘርፍ ሥራዎችን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የመሥራት ደረጃን ለማሻሻል በትኩረት መሥራት፣ የምርምር ሥራ ውጤቶችና የተላመዱና የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ የማሸጋገር ሥራ አጠናክሮ መሥራት፣ ከኦዲት ግኝት የጸዳ ተቋም ለመሆን በትኩረት መሥራት፣ የገቢ ማመንጫ አማራጮችን በማበራከትና አሠራሮችን በማሻሻል ገቢን ማሳደግ፣ ነባር የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና አዲስ የተጀመሩት በብቃት እንዲሠሩ ትኩረት ሰጥቶ መደገፍ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሠረት የሠራተኛ ምደባ ሥራን በትኩረት ማከናወን በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

‹‹Ethiopian Higher Education, Leadership, Management and Governance Training for Public Higher Education Institution Leaders /LMG/›› በሚል ርእስ በተሰጠው የ10 ቀናት ሥልጠናና አሜሪካ ሀገር በሚገኙ በቴክሳስ/Texas/፣ ኦክላሆማ/Oklahoma/ እና ኦህዮ/Ohio/ ዩኒቨርሲቲዎች የልምድ ልውውጥ ላይ የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን በቆይታቸው ከተቋማቱ አደረጃጀት፣ ከመምህራን ደመወዝ አከፋፈል፣ ከስፖርትና መዝናኛ መሠረት ልማቶች አሠራርና አጠቃቀም፣ ከበጀት ምንጭ፣ ከምድረ ግቢ ውበት፣ የቀድሞ ምሩቃን አደረጃጀትና ሚና፣ ከኮሚዩኒኬሽንና ብራንዲንግ አንጻር የተመለከቷቸውን አዳዲስ ልምዶችንና አሠራሮችን የተመለከተ ገለጻ ለካውንስሉ በማቅረብ ልምድ አጋርተዋል፡፡