የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ‹‹መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!!›› በሚል መሪ ቃል 18ኛውን ሀገር አቀፍ የነጭ ሪባን ቀን ከኅዳር 16/2016 ዓ/ም ጀምሮ በማክበር ላይ ይገኛል፡፡ አከባበሩ እስከ ታኅሣሥ 1/2016 ዓ/ም የሚቆይ ሲሆን በሁሉም ካምፓሶች የሚገኙ ተማሪዎችንና የአስተዳደር ሠራተኞችን በማሳተፍ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት መንስኤና የሚያስከትለው ችግር ላይ አጠር ያለ ሥልጠና፣ ውይይት እንዲሁም የተለያዩ ሥነ ጽሑፎች በተማሪዎች እየቀረቡ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የነጭ ሪባን ቀን ወንዶች በሴቶች ላይ የሚደርስ ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከል አጋርነታቸውን የሚገልጹበት ሲሆን በማኅበረሰቡ ዘንድ ሥር የሰደደና የተዛባ የሥርዓተ ጾታ አመለካከት ችግርን ከመቅረፍ አንጻርም የግንዛቤ መፍጠር ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት