በ2015 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት በማምጣት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2015 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ታኅሣሥ 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ስለሆነም ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

  • የ8 ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
  • ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
  • የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
  • የፓስፖርት መጠን (Passport Size) የሆኑ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፎች እና
  • አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ

በመያዝ ሁሉም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ዓባያ ካምፓስ፣ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የስም ዝርዝራችሁ ከፍደል ተራ “A” እስከ “S” የሚጀምሩ በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው በጫሞ ካምፓስ እና የስም ዝርዝራችሁ ከፍደል ተራ “T” እስከ “Z” የሚጀምሩ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው በሳውላ ካምፓስ በአካል  ቀርባችሁ እንዲትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡

 ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል፡፡

 የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት