ረ/ፕ ታደሰ አብርሃም ከአባታቸው ከአቶ አብርሃም ወርቁ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዴ ተሰማ በቀድሞው ወሎ ክፍለ ሀገር በደሴ ዙሪያ ወረዳ መስከረም 3/1953 ዓ.ም ተወለዱ፡፡  ረ/ፕ ታደሰ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅግጅጋ እና በአፊሲን እንዲሁም የመለስተኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጋምቤላ፣ ጐሬና ባዕደማርያም ላቦራቶሪ ት/ቤቶች ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

ረ/ፕ ታደሰ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ1974 - ጥቅምት 29/1978 ዓ.ም በፍልስፍና ትምህርት ዘርፍ ተካታትለው ተመርቀዋል፡፡
 
ረ/ፕ ታደሰ በአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመጀመሪያ ተቀጣሪ በመሆን ከታኅሣሥ 24/1978 ዓ.ም - ነሐሴ 30/1982 ዓ.ም በሌክቸረር I አካዳሚክ ማዕረግ፣ ከመስከረም 1/1983 ዓ.ም - ነሐሴ 30/1985 ዓ.ም በሌክቸረር II አካዳሚክ ማዕረግ፣ ከመስከረም 1/1986 ዓ.ም - ታኅሣሥ 30/1988 ዓ.ም በሌክቸረር III አካዳሚክ ማዕረግ፣ ከጥር 1/1988 ዓ.ም - ሰኔ 30 /1999 ዓ.ም በሌክቸረር አካዳሚክ ማዕረግ እና ከሐምሌ 1/1999 ዓ.ም - መስከረም/2012 ዓ.ም በረዳት ፕሮፌሰር አካዳሚክ ማዕረግ ዩኒቨርሲቲውን አገልግለዋል፡፡
 
ረ/ፕ ታደሰ አብርሃም በደረሰባቸው የጤና መታወክ ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 11/2016 ዓ/ም በተወለዱ በ63 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ረ/ፕ ታደሰ አብርሃም ባለትዳር እና የሁለት ወንድ እና የሦስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡  
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በረ/ፕ ታደሰ አብርሃም ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት