የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ እየተሠራ ያለውን የከተማ ግብርና፣ የዓሣ እርባታ እና የሕፃናት ማቆያ ግንባታ ጥር 22/2016 ዓ/ም ጎብኝተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እንደገለጹት በኮሌጁ ለምርምር፣ ለሠርቶ ማሳያና ለገቢ ማስገኛ እየተሠሩ ያሉት ሥራዎች ውጤታማና ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡ ከውኃ ምኅንድስና በመቀጠል የግብርና ሳይንስ የዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስክ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዝደንቱ በኮሌጁ የሚከናወኑት የግብርና ሥራዎች በዘርፉ ምሁራን በተጠና ሳይንሳዊ መንገድ የሚሠሩ በመሆኑ ከፍተኛ ውጤት የሚገኝባቸውና ለምርምር ሠርቶ ማሳያ የሚያገለግሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደጋፌ አሰፋ በኮሌጁ በቅድመና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመማር ማስተማር ሂደቱ በተግባር የተደገፈ መሆኑን ጠቁመው በከተማ ግብርና የተለያዩ ፍራፍሬዎችና አትክልቶችን በማልማት ውብና ማራኪ አካባቢ መፍጠር እንዲሁም ምርቱን ለማኅበረሰቡ በቅናሽ ዋጋ ለሽያጭ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ዲኑ አሁን ላይ የተፈጥሮ ዝናብና የመስኖ ውኃን በመጠቀም በ10 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶችና አዝርእት በመዝራት ውጤታማ ምርት እየተገኘ ነው ብለዋል፡፡

በምልከታው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ፣ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን፣ የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደጋፌ አሰፋና ሌሎች የኮሌጁ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት