በ17/08/2016 ከ8:00 ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በኢንተርፕርነርሽፕ ዙሪያ ያተኮረ ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል። በዝግጅቱ ላይ ታዋቂው የቢዝነስ አማካሪ እና ደራሲ ዶ/ር ወሮታው በዛብህ ተገኝተው የኢንተርፕርነርሽፕ የተግባር ተሞክሯቸውን ያካፍላሉ። በተጨማሪ በዕለቱ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ይካሄዳል። የተሻለ ሃሳብ ያቀረቡ ተማሪዎችም ይሸለማሉ:: ስለሆነም ሁሉም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ሁነት ላይ እንድትገኙ የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት