- Details
በጫሞ ሐይቅ ረግረጋማ ስፍራና የሐይቁ የላይኛው ተፋሰስ አካል በሆነው ጌዣ ደን ውስጥ ምርምርን መሠረት ያደረገ የመልሶ ማልማት የሙከራ /Pilot/ ፕሮጀክት አካላዊና ሥነ-ሕይወታዊ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የሙከራ ፕሮጀክቱ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከሮማንና ኃይለማርያም ፋውንዴሽን፣ ከቤልጂየሙ ኬዩሊዩቨን ዩኒቨርሲቲ/KU Leuven University/ እና ቢኦኤስ+/BOS+/ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር የተጀመረ ሲሆን ከጀርመን ልማት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለሚሠራው ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ፕሮጀክት እንደ ማሳያ የሚያገለግል ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የጫሞ ሐይቅ ተፋሰስ የሙከራ ፕሮጀክት አካላዊና ሥነ-ሕይወታዊ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ ነው
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከአርባ ምንጭ ከተማ ሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከከተማው አስተዳደር ለተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች የአመራርነት ሥልጠና ግንቦት 4/2015 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ሴት የሥራ ኃላፊዎች የአመራርነት ሥልጠና ተሰጠ
- Details
Arba Minch University Senate promoted six academic staff to Associate Professorship Academic Rank position on May 11/2023. Click here to see more pictures!
Read more: AMU Senate Promotes Six Staff to Associate Professorship Academic Rank Position
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በኮንሶ ዞን በካራት እና ኮልሜ ክላስተር እንዲሁም በአሌ ልዩ ወረዳ በኦላንጎ በሚገኙ የነጻ ሕግ ድጋፍ መስጫ ማእከላት ላይ ግንቦት 3/2015 ዓ/ም የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርቲ ሕግ ት/ቤት በኮንሶ ዞንና አሌ ልዩ ወረዳ የሚገኙ የነጻ ሕግ ድጋፍ መስጫ ማእከላት ላይ የመስክ ምልከታ አካሄደ
- Details
የ45 ቀን ዕድሜ ያላቸው 2,000 ሳሶ ብሮይለር ብሪድ/Saso Broiler Breed/ ዝርያ ጫጩቶችን በመረከብ ሥራ የጀመረው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ምርምር ማእከል ከሚያዝያ 24/2015 ዓ/ም ጀምሮ 1,800 የእርድና እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ለሽያጭ አቅርቦ እየሸጠ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ምርምር ማእከል 1,800 ዶሮዎችን ለሽያጭ አቀረበ

