ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አኳያ - የትምህርት ፕሮግራም
ለሁሉም ትምህርት ክፍሎች፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት በሙሉ
በ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችን በምርጫው መሳተፍ ይችሉ ዘንድ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠ አቅጣጫ ከሰኔ 7-21 ያለው ጊዜ የገጽ ለገጽ ትምህርት አይኖርም፡፡ ነገር ግን በቀጣይ የሚኖረን ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
- የ2012 1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራም ምደባችሁ መሠረት ከወዲሁ አስፈላጊውን ጨርሳችሁ ወደ ካምፓሶቻችሁ (የጤና፣ የግብርና እና የማኅበራዊና ስነ-ሰብ ሳይንስ ተማሪዎች) እንድትሄዱና በ22/10/2013 በየተመደባችሁበት ትምህርት ክፍል ትምህርት ይጀመራል፡፡
- ሌሎች መደበኛ ተማሪዎች የ2013 1ኛ መንፈቅ የክፍል ትምህርት በ05/10/2013 የሚጠናቀቅ ሲሆን ማጠቃለያ ፈተና ከ22/10/2013 ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- የ2013 አዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ከ21/10/2013 በኋላ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ምርጫ ለመምረጥ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ከሰኔ 8 ቀን እስከ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት የማይኖር ሲሆን በዚሁ ጊዜ ተማሪዎች ወደመጡባቸው አካባቢዎች በመሄድ ምርጫ ላይ ይሳተፋሉ::
- ትምህርት ዝግ በሆነበት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ መቆየት የሚፈልጉ መደበኛ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ሕግና ደንቦችን በማክበር መቆየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ሌሎች ኢ-መደበኛ ትምህርቶች የተከታታይ (Extenstion) እና ሳምንት መጨረሻ (Weekend) ተማሪዎች ከምርጫው በኋላ በሚኖረው አንድ ሳምንት (ከሰኔ 15 እስከ 20/2013 ዓ.ም ብቻ) የመማር ማስተማር ሂደት አይኖርም፡፡
- ሁሉም የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ ከምርጫው በኋላ በሚኖረው አንድ ሳምንት (ከሰኔ 15 እስከ 20/2013 ዓ.ም ብቻ) ብቻ ትምህርት በገጽ ለገጽ ምትክ በኦንላይን (Virtual) አማራጭ ይካሄዳል፡:
በመሆኑም የሚመለከታችሁ የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ማኅበረሰቡ በሙሉ ከላይ በተጠቀሰው መሠረት አስፈላጊውን ዝግጅትና ክትትል በማድረግ እንዲፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዪኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት