የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ሀገራዊ ሥልጠና ተጀመረ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህር ተቋማት ሀገራዊ ሥልጠናን ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ከጥቅምት 2/2010 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት መስጠት ጀምሯል፡፡

ሥልጠናው በየካምፓሶቹ የሚካሄድ ሲሆን የውጤታማነት ትግበራ ስኬት አሠራር፣ ሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር፣ ሴርኩላሪዝምና ህገ-መንግሥት እና የዩኒቨርሲቲው የ2010 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡ አጠቃላይ ኤሬንቴሽንም የሚሰጥ ይሆናል፡፡