በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የስነ-ትምህርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል በጎልማሶች ትምህርትና ማህበረሰብ ልማት የቅድመ ምረቃ መርሃ-ግብር ለመክፈት የሚያስችለውን ስርዓተ-ትምህርት ግምገማ ሰኔ 22/2007 / አካሄደ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን / ተሾመ ይርጉ የመርሃ-ግብሩ መከፈት ለጎልማሶች የሚሰጠውን ትምህርት በተደራጀና በተቀላጠፈ አኳሃን ተግባራዊ ለማድረግና በዘርፉ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ሃይል ውስንነት ለመቅረፍ እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / ፈለቀ ወልደየስ በጎልማሶች ትምህርትና በማህበረሰብ ልማት ተደራሽነትና ጥራት የትምህርት ክፍሉ መከፈት የጎላ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው እየሰጠ ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት የማህበረሰቡን የትምህርት ፣የጤና እንዲሁም የግብርና ክህሎትና ዕውቀት በማሳደግ የአኗኗር ዘይቤን ለማዘመን እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

ስርዓተ-ትምህርቱን ያዘጋጁት የስነ-/ ሳይንስ / ክፍል መምህራን / ይስሃቅ ደገፉ፣መ/ ዘላለም ዘካሪያስ እና / ተፈራ ገባባ ሲሆኑ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ (Need Assessment) በጋሞ ጎፋ ፣በወላይታ ፣በደቡብ ኦሞ እና በሰገን ህዝቦች ዞኖች መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

ግምገማውን ያካሄዱት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥናትና ምርምር ተቋም ተመራማሪና መምህር / ፍርዴሳ ጀበሳ እና በዩኒቨርሲቲው የስርዓተ-ትምህርትና የመምህራን ሙያ ልማት ጥናት / ክፍል መምህር / ደሱ ዊርቱ ናቸው፡፡የግምገማው ተሳታፊዎችም መዳበርና መካተት ይኖርባቸዋል ያሏቸውን ሀሳብ አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡ከተሳታፊ ባለድርሻ አካላት መካከል የጋሞ ጎፋ ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ እንዳለ አንዱ ሲሆኑ የመርሃ-ግብሩ መከፈት ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ ስራዎችን ለሚሰሩ መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የሰው ሃይል እንዲያሟሉ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ልዩ ረዳት / ዳምጠው ዳርዛ በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ኮሌጁም ሆነ የት/ ክፍሉ ግምገማው እንዲከናወን ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን ሚና መጫወታቸው የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡