- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባባር ‹‹Building Information Management/BIM›› በሚል ርእስ ለአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ እና ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች መምህራን፣ ለዩኒቨርሲቲው ፋሲሊቲ አስተዳደርና የግንባታ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ከጥር 13 - 30/2016 ዓ/ም የግንባታ ሞዴሊንግ ቴክኖሎጂን አስመልክቶ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የአርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ የፀረ ሙስናና ሥነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለጫሞ፣ ዓባያና ሳውላ ካምፓሶች አዲስ ገቢ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዲስፕሊን መመሪያ ላይ ከጥር 25 - የካቲት 02/2016 ዓ/ም የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዲስፕሊን መመሪያ ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው
- Details
ዩኒቨርሲቲው ከአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የማንጎ ማውረጃ ቴክኖሎጂ ጥር 28/2016 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ኦቾሎ ላንቴ ቀበሌ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ለሙከራ አቅርቧል፡፡ የቴክኖሎጂዎቹን አጠቃቀም አስመልክቶ በባለሙያዎች ገለጻ በማድረግ ሁለት የማውረጃ መሣሪያዎችን በቡድን የተከፈሉ አርሶ አደሮች የተረከቡ ሲሆን ከአርሶ አደሩ የሚመጣውን ግብረ መልስ ተከትሎ ማሻሻያ ታክሎ በስፋት ለማዳረስ እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማንጎ ማውረጃ ቴክኖሎጂን ለአርሶ አደሩ ለሙከራ አቀረበ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በምርምር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለተወጣጡ የኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች ከጥር 23 - 26 ለአራት ተከታታይ ቀናት የጂአይኤስ አጠቃቀም ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና ተመራማሪዎች በጂአይኤስ/GIS/ ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣንና ከጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር “የጋሞ ዱቡሻ እና የዱቡሻ ዎጋ˝ ሥርዓት የጥናትና ምርምር ማስጀመሪያ የማኅበረሰብ ንቅናቄ መድረክ ጥር 25/20/16 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: “የጋሞ ዱቡሻ እና የዱቡሻ ዎጋ" የጥናትና ምርምር ማስጀመሪያ የማኅበረሰብ ንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ