የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት የአምሳለ ፍርድ ቤት ፍጻሜ ውድድር ጥር 23/2016 ዓ/ም ያካሄደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ውድድር ኢትዮጵያንና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን በመወከል በታንዛንያ አሩሻ በተደረገው ጠቅላላ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ውድድር ተሳትፈው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የፎረንሲክ ሜዲስንና ቶክሲኮሎጂ ስፔሻሊቲ ተማሪዎች ከታኅሣሥ 18 - ጥር 24/2016 ዓ/ም በሁለት ዙሮች የፎረንሲክ ናሙና ምርመራ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በኢኮኖሚክስ ት/ክፍል በ“Development Economics” ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሰለሞን ከበደ  የካቲት 01/2016 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ  የ3 ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ መግቢያ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ያቀርባል፡፡ 

የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት የባህሪ ማሻሻያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከ“International Youth Fellowship” ጋር በመተባበር በአዕምሮ ውቅር (Mindset) ዙሪያ ከደቡብ ኮሪያ በመጡ አሠልጣኞች ለጫሞ ካምፓስና ለዋናው ግቢ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች፣ ለመደበኛና ኢ-መደበኛ ሪሜዲያል ተማሪዎች እና ለባይራ አዳሪ 2ኛ ደ/ት/ቤት ተማሪዎች  ጥር 18/2016 ዓ/ም የአዕምሮ ውቅር/Mindset/ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡