አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ2010 የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ 5,833 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ከመስከረም 27-28/2010 ዓ.ም ተቀብሏል፡፡ ከአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ መካከል 3,340ዎቹ ወንዶች ሲሆኑ 2,493ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

በኢንጂነሪንግ ሣይንስ 1,535፣ በኮምፒውተር ሣይንስ 345፣ በተፈጥሮ ሣይንስ 1036፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ 1,100፣ በማኅበራዊ ሣይንስና ሥነ-ሰብ እና በፔዳጎጂና ሥነ-ባህርይ ሣይንስ 860፣ በህክምና 120፣በማኅበረሰብ ጤና 60፣ በሌሎች የጤናሣይንስ ትምህርቶች 275፣ በህግ 60 እና በግብርና ሣይንስ 442 ተማሪዎች ተመድበዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እንኳን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በሠላም መጣችሁ እያለ መጪው የትምህርት ዘመን የሠላምና የስኬት እንዲሆን ይመኛል፡፡