ውድና የተከበራችሁ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በሙሉ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተገባዶ የመጀመሪያዉ ደረጃ የዉሃ ሙሌት በመጠናቀቁ በድጋሚ እንኳን ደስ አለን፡፡ ቀሪዉን የግንባታ ሥራ ለማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ተነሳሽነት በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማገኅበረሰብም ቀደም ሲል ስናደርግ እንደነበርነዉ ሁሉ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይም የዜግነት አሻራችንን ማስቀመጡን መቀጠል ይጠበቅብናል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት ይህንን ይጫኑ

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲያችን ካዉንስል በ01/12/2012 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ በመወያየት የዩኒቨርሲቲዉ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በየሚሠሩበት ካምፓስና ትምህርት ክፍል በኩል በሚመቻች  መንገድ በመወያየት የቦንድ ግዥ ለመፈጸም ዝግጅት እንዲደረግ አስተያየት ቀርቧል፡፡

በዚህም መሠረት በየካምፓሶቻችሁ በኩል በሚተላለፍ ጥሪ መሠረት በቦንድ ግዥ እንዲትሳተፉ ዩኒቨርሲቲው በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ መግባባት ተምሳሌት!

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት