ማክሰኞ ኅዳር 08/2013 ዓ/ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል በአገር ደረጃ እንዲካሄድ ለቀረበው አገራዊ ጥሪ መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በየካምፓሱና በያለበት በመቆም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን አጋርነት በተግባር አረጋግጧል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በሁሉም የሀገራችን ዳር ድንበሮች በግምባር ቀደም ተሰላፊነት ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ለሕዝባችን ክብር የሚከፍለውን መሥዋዕትነት በመዘከርና በማድነቅ ለ1 ደቂቃ ቀኝ እጅን በደረት ላይ በማድረግ እንዲሁም ለ 1 ደቂቃ ደግሞ ያለማቋረጥ በማጨብጨብ ለሠራዊቱ ክብር የመቆም ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የሀገር ክብርና ኩራት ለሆነው መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገው የገንዘብና የደም ልገሳ መርሃ ግብር ሐሙስ ከጧቱ 02፡30 ጀምሮ በሁሉም ካምፓሶች በንቁ ተሳትፎ የሚከናወን ይሆናል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት