የዩኒቨርሲቲው የባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም በተቋሙ ተመራማሪዎች፣ በማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ መምህራንና በድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የቀረቡ የምርምር ንደፈ ሃሳቦችን ሚያዝያ 15/2013 ዓ/ም ገምግሟል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በመድረኩ 30 የምርምር ንድፈ ሃሳቦች ለግምገማ የቀረቡ ሲሆን "ቋንቋን ማቆየትና መተው ተጽዕኖ ትንተና በደራሼ ቋንቋ ተተኳሪነት"፣ "የቃላት ዘዬዎች ስነ-ልሳናዊ ባህሪ ትንተና በጋሞ ብሄረሰብ ጋሞኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ተተኳሪነት"፣ "የድምጽ አወጣጥ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ እንዴት ግልጋሎት ይሰጣል? እንዴት ደግሞ ከማኅበራዊ ሕይወት ጋር ይቆራኛል?" የሚሉት ከቀረቡት ንድፈ ሃሳቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይድ አህመድ እንደገለጹት ከዚህ በፊት ተቋሙ ሦስት ጊዜ የምርምር ንድፈ ሃሳብ ግምገማ መድረጉን አስታውሰው የአሁኑን ልዩ የሚያደርገው በተቋሙ ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የምርምር ንድፈ ሃሳብ ተዘጋጅቶ ሊቀርብ መቻሉ ነው ብለዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት