በአርባ ምንጭ ዪኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ትምህርት ክፍል ከእንግሊዝኛ ቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር <<English for Secretaries>> በሚል ርዕስ ለቢሮ ፀሐፊዎችና ረዳቶች በዋናዉ ግቢ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ሥልጠናው እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ እንግዶች ወደ ቢሮ ሲመጡ በጥሩ ሥነ-ምግባር በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተናገድ፣ የስልክ አቀባበልና ምላሽ አሰጣጥ፣ በፖስታ ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ አድራሻ አጻጻፍ፣ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ እንግዶችን ለኃላፊ ወይም ለሌላ ሰው ማስተዋወቅ እና ፎርም በእንግሊዝኛ መሙላት በሚሉ ይዘቶች እንደሚሰጥ የሥልጠናው አስተባባሪ ዶ/ር መለሰ መንገሻ ገልጸዋል፡፡ የሥልጠናዉ ዋና ዓላማ የቢሮ ፀሐፊዎችና ረዳቶች የእንግሊዝኛ ቋንቋ የንግግር ክሂሎታቸዉን ለማዳበር የታሰበ መሆኑን ዶ/ር መለሰ አክለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዉ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል መምህርና አሰልጣኝ መ/ር ማንጉዳይ ማርጮ በበኩላቸው እንደገለጹት ሥልጠናው የቢሮ ፀሐፊዎችና ረዳቶች የእንግሊዝኛ ቋንቋ የንግግር ችሎታቸውን በተገቢው ሁኔታ በመጠቀምና ከዚህ በፊት የነበሩባቸውን ችግሮች በከፊልም ቢሆን በመቅረፍ ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ደምበኞች የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንድችሉ አቅም የሚፈጥር ነው፡፡

የፕሬዝደንት ጽ/ቤት የቢሮ ረዳት የሆነችው ወ/ሮ ለምለም ታደሰ ስለ ሥልጠናው ስትገልጽ ሥልጠናው ለኔ በጣም ጥሩ ነበር ብላለች፡፡ በተጨማሪም ሥልጠናው የሚያነቃቃና እንግሊዝኛ ቋንቋን በድፍረት ለመጠቀም የሚያበረታታ ሆኖ ማግኘቷን እንዲሁም ሥልጠናው ቀጣይነት ቢኖረዉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዋን በሂደት በጥሩ ሁኔታ ለማሻሻል እንደምትችል መገንዘቧን ወ/ሮ ለምለም ተናግራለች፡፡

በሥልጠናው ከሳውላ ካምፓስ ከ5ቱ ካምፓሶች የመጡ ሠልጣኞች የተሳተፉ ሲሆንበሥልጠናው ለተገኙት የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት