የዩኒቨርሲቲው ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከሆላንድ ማስትሪች ዩኒቨርሲቲ ጋር የ3ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞችን በጋራ ለመክፈት ጳጉሜ 2/2013 ዓ/ም ስምምነት ተፈራርሟል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ  

በበይነ መረብ የተከናወነው ስምምነት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በተማሪዎች የትምህርት ልምድ ልውውጥ ዙሪያ አብሮ ለመሥራት እንዲሁም የ3ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞችን በጋራ ለመክፈት ያስችላል፡፡

የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ሽብሩ እንደገለጹት ኮሌጁ ውጪ ሀገር ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ፕሮግራሞችን የመክፈትና ተማሪዎችን የማስተማር ዕቅድ ይዞ እየሠራ ነው፡፡ ከማስትሪች ዩኒቨርሲቲ ጋር በፈጸሙት ስምምነት መሠረትም በኅብረተሰብ ጤናና በሌሎች ፕሮግራሞች በዓመት 6 የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ በጋራ ያስተምራሉ፡፡ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ ተማሪዎችን በመመልመልና የልምድ ልውውጥ በማድረግ ወደ ትምህርት እንዲገቡ የሚመቻች መሆኑን ዶ/ር ታምሩ ተናግረዋል፡፡

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ሽብሩ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እንዲሁም የት/ክፍል ኃላፊዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

 

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት