አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን 5 ሺህ ያህል ተማሪዎች በ3ኛ፣ በ2ኛ እና በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ-ግብሮች መስከረም 29/2014 ዓ.ም በዓባያ ካምፓስ ስቴዲዬም ለ34ኛ ዙር እንዲሁም የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎችን መስከረም 30/2014 ዓ.ም በሳውላ ካምፓስ ለ4ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

መስከረም 29/2014 ዓ/ም በዓባያ ካምፓስ በሚካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ የክብር፣ ተጋባዥና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የምሩቃን ቤተሰቦችና የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አባላት የሚገኙ ሲሆን ሥነ-ሥርዓቱም በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ከጧቱ 03፡00 – 05፡00 ሰዓት የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም ተመራቂዎችን ጨምሮ በ34 ዙሮች ከ66,000 በላይ ብቃት ያላቸው ምሩቃንን በማፍራት ለሀገራችን ልማትና ዕድገት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣና እያበረከተ ያለ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡

      የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት