የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ “አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ!” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ አሸባሪው የሕወኃት ቡድን በፈጸመው ዘግናኝና አሰቃቂ ጥቃት የተሰው የሀገር መከላከያ አባላትን በማሰብ የዝክርና የሂሊና ፀሎት ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በሠራዊቱ ላይ ጥቃት ከተፈፀመበትና መንግሥት የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ፣ ደም በመለገስ ከሠራዊቱ ጎን መሆኑን እያሳየ የቆየ ሲሆን በዛሬው ሀገራዊ መርሃ-ግብርም የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሁሌም ከሠራዊቱ ጎን እንደሚቆም “አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ!” የሚለውን የዕለቱን መሪ ቃል በማሰማት ያረጋገጠበት ነው፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት