በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሀገር በቀል 3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም በ“Irrigation Engineering”፣ “Ground Water Engineering”፣ “Water Supply and Sanitary Engineering” ለመማር ያመለከታችሁ አመልካቾች እና የመጀመሪያውን ምልመላ ያለፋችሁ አመልካቾች የ“Home-Grown Collaborative PhD Programs (HCPP)” ፕሮጀክት በአሁኑ ጊዜ ባለመኖሩ በዩኒቨርሲቲው መደበኛ የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም መቀጠል የምትፈልጉ የመጨረሻውን የመግቢያ ፈተና በቀን 30/3/2014 ዓ.ም የሚሰጥ ስለሆነ ፍላጎቱ ያላችሁ ከላይ በተጠቀሰው ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ በአካል በመገኘት እንድትፈተኑ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፣

  • የHCPP ፕሮጀክት የሚቀጥል ከሆነ በቀጥታ ወደዛ ፕሮግራም የምናዛውራችሁ መሆኑንም ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ በተጨማሪም እንደ ማንኛዉም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ የዶርሚተሪ አገልግሎት እናመቻቻለን፡፡

አርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት