በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ በሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ የተከበረው ዓለም አቀፍ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ8ኛ ጊዜ ‹‹በሥነ ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ!›› በሚል መሪ ቃል ኅዳር 21/2014 ዓ/ም በተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ተከብሯል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ወርቁ እንደገለጹት ተማሪዎች ወጣቶችና ነገ ወደ ሥራ ዓለም የሚሠማሩ በመሆናቸው የሥነ-ምግባር ግንባታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሥነ-ምግባር ያልተገነባ ትውልድ ለሀገርም ለቤተሰብም አስቸጋሪ ስለሆነ በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ በመገንባት ራስንም ሆነ ተቋሙን ከሙስና የፀዳ ማድረግ የበዓሉ ዋና ዓላማ መሆኑን አቶ ዮሴፍ ተናግረዋል፡፡

የጥያቄና መልስ ተወዳዳሪ ተማሪ ኤደን አማረ ከውድድሩ ስለ ሙስና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ዕውቀት ማግኘቷን ገልጻለች፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች በመልካም ሥነ-ምግባር በመታነፅ ለቤተሰብም ሆነ ለሀገር የምንጠቅም መሆን ይጠበቅብናል ብላለች፡፡

በጥያቄና መልስ ውድድሩ ከ1ኛ- 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት