በማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ሶሲዮሎጂና ሶሻል አንትሮፖሎጂ ት/ክፍል በቅርቡ ለመክፈት በዝግጅት ላይ ያለውን የሶሻል አንትሮፖሎጂ የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም አስመልክቶ ሊያጋጥሙ በሚችሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ ጀርመን ሀገር ከሚገኘው ጎቲንገን ዩኒቨርሲቲ ከመጡት ዶ/ር ክርስቲና ጋርበርት ጋር መጋቢት 02/2014 ዓ/ም ውይይት አድርጓል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሙሉጌታ ደበሌ እንደገለጹት ለሚከፈተው የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም የውስጥና የውጪ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሂዷል፡፡ ፕሮግራሙን ለመክፈት በዋናነት የአማካሪ መምህራንና የመጻሕፍት እጥረት እንዳለ ገልጸው በውይይታቸው ከዚህ ቀደም በተደረገው የጋራ ስምምነት መሠረት ነባር ፕሮፌሰሮች ለማስተማርና ለማማከር ከጎቲንገን ዩኒቨርሲቲ እንዲመጡ እንዲሁም የመጻሕፍት ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በጎቲንገን ዩኒቨርሲቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህርት የሆኑት ዶ/ር ክርስቲና ጋርበርት ዩኒቨርሲቲያቸው ከአንድ ሺህ በላይ መጻሕፍትን ለት/ክፍሉ ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጸው በፕሮግራሙ ላይ የሚያጋጥሙ ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት እንዲሁም የተማሪና የመምህራን ልውውጥን በተመለከተ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት