በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ‹‹የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለዘላቂ ልማት እና ተግዳሮቶች/3rd National Conference on Innovation and Challenges in Engineering and Technology for Sustainable Development›› በሚል ርዕስ 3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ዓውደ ጥናት ከግንቦት 26 - 27/2014 ዓ/ም ድረስ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በዓውደ ጥናቱ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና የምርምር ማዕከላትና ተቋማት በሚመጡ ተመራማሪዎች 22 ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡ ሲሆን በፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ ከመረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ፣ ከኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የመጡ እንግዶችና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች እና መምህራን የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት