የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 23/2014 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ መርሃ ግብር በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት፣ በሳምንት መጨረሻ እና በተከታታይና ርቀት እንዲሁም በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 2,540 ተማሪዎችን ቅዳሜ ሰኔ 25/2014 ዓ/ም እና እሁድ ሰኔ 26/2014 ዓ/ም እንዲመረቁ ወስኗል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 657ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ 

የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ አዲሱ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ እና የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት