የ"CAF" "D" License" የእግር ኳስ አሠልጣኝነት ሥልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚና ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ከደቡብ ክልል ለተወጣጡ በሥራ ላይ ላሉ አሠልጣኞች የአሠልጣኝነት ሥልጠና ከኅዳር 20 - 29/2015 ዓ.ም እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ሥልጠናው በአህጉር ደረጃ ከፌዴራል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተመደቡ አህጉር አቀፍ አሠልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን አሠልጣኖቹም በተሳታፊ ዞኖች ታዳጊ ሕፃናት ፕሮጀክቶችን እያሠለጠኑ የሚገኙና ሥራ ላይ ያሉ ሠልጣኖችን ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በተጨማሪም ሥልጠናው መሠረታዊ ክህሎትንና ጾታን ባማከለ ሁኔታ የአፍሪካ ስፖርት ኮንፌዴሬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን ዕውቀት መሠረት ያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በፕሮግራሙ ከፌዴራል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የእግር ኳስ ፌዴሬሽንና ከተለያዩ የደቡብ ክልል ዞኖች የጋሞ ዞንን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በሥልጠናው ማጠቃለያ ለሠልጣኞች የ"CAF" "D" License" የእግር ኳስ አሠልጣኝነት ሠርተፊኬት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት