የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ለ1 ዓመት የ"Pre-Engineering" ተማሪዎች የዲፓርትመንት ምርጫ ገለፃ ጥር 9/2015 ዓ/ም አድርገዋል፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉነህ ለማ እንደተናገሩት ገለፃው በዋናነት ተማሪዎች በሀለቱም ኢንስቲትዩቶች ስር ስለሚገኙት ፋከልቲዎች ሙሉ መረጃ በማግኘት የፍላጎታቸውን ዲፓርትመንት ለማግኘት በምርጫ የሚወዳደሩበትን ግንዛቤ የሚፈጥር ነው፡፡

የዋና ግቢ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች አስተባባሪ መ/ር ደሞዜ እሸቴ ገለፃው ለ1 ዓመት የ"Pre-Engineering"ተማሪዎች የ1 ዓመት 2 ሴምስተርን አጠናቀው 2 ዓመት በምርጫ ውድድር ያሸነፉትን ዲፓርትመንት የሚገቡ በመሆኑ ተማሪዎች ስለዲፓርትመንት ምርጫ ውድድር ሙሉ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ተማሪዎችን ለማገዝ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ መ/ር ደሞዜ በገለጻው በዋና ግቢና በሳውላ ካምፓስ ስር ስለሚገኙ ፋከልቲዎች እንዲሁም ስለእያንዳንዱ ትምህርት ክፍል ዓላማና ምንነት የማሳወቅና ጠቃሚ ማብራሪያዎችን የመስጠት ሥራ ተከናውኗል፡፡ በዚሁ መሠረት ተማሪዎች በፍላጎታቸው ተመስርተው የሚፈልጉትን ዲፓርትመንት ለመምረጥ በምርጫ እንደሚወዳደሩ መ/ር ደሞዜ ጠቁመዋል፡፡

በፕሮግራሙ የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር፣ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር፣ የፋከልቲ ዲኖችና ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት