በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በእንስሳት ሳይንስ ት/ክፍል በእንስሳት ስነ-ምግብ ‹‹Animal Nutrition›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ዕጩ ዶ/ር ጌታቸው አብርሃም መጋቢት 28/2015 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፋቸውን የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ አዲሱ አዳራሽ ያቀርባሉ፡፡

ዶ/ር ጌታቸው አብርሃም በኮሌጁ ታሪክ የመጀመሪያው የ3ኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ሲሆኑ የመመረቂያ ጽሑፋቸውንም ‹‹INDIGENOUS LEGUME FODDER TREES AND SHRUBS IN GAMO ZONE, ETHIOPIA: EMPHASIS ON ECOLOGICAL VALUE, NUTRITIONAL QUALITY AND METHANE EMISSION POTENTIALS›› በሚል ርዕስ አከናውነዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት