የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-መጻሕፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ"Anti-Plagiarism Software and Subscribed Journals" ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ግንቦት 15/2015 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ቴክኖሎጂ መረጃን በቀላሉ ከመቀበልና ከማሰራጨት ባሻገር በርካታ ጥቅሞች ያለው በመሆኑ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ይህንን ሶፍትዌር መጠቀም መቻሉ የትምህርት ጥራትና የምርምር ሥራዎች ደረጃን ከፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የቤተ-መጻሕፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ቱምሳ ሶፍትዌሩ ሌላ ቦታ የተሠሩ ምርምሮች እንዳይሰረቁና ደግመው እንዳይሠሩ በተለየ መንገድ የሚከላከል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሶፍትዌሩ ለትምህርት ጥራት ትልቅ ሚና ያለው ሲሆን ተማሪዎች የምርምር ሥራቸውን  በራስ ተነሳሽነት እንዲሠሩ የሚያበረታታ እንደሆነም አቶ ሲሳይ ጠቅሰዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች፣የኮሌጅ ዲኖችና መምህራን ተገኝተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት