በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኮምፒውቲንግና ሶፍትዌር ኢንጂነርንግ ፋከልቲ በ “Computing and Information Technology” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል  ሰኔ 02/2015 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ ከ8፡30 ጀምሮ  የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናዉ ግቢ መግቢያ አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ ያቀርባል፡፡

ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል በኢንስቲትዩቱ ታሪክ የመጀመሪያዉ  የ3ኛ ዲግሪ ምሩቅ ሲሆን“OFFLINE HANDWRITTEN AMHARIC CHARACTER RECOGNITION USING DEEP LEARNING” በሚል ርዕስ ያከናወነውን የመመረቂያ ጽሑፍ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት