ወ/ሮ ታየች በለጠ ከአባታቸው አቶ በለጠ ማሞ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ጂንጌ አጉርሽ በቀድሞው ጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር አርባ ምንጭ ከተማ መስከረም 20/1965 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ኩልፎ 1ኛ ደረጃ እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ ወ/ሮ ታየች መስከረም 11/2004 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለደረጃ 3 ሊያበቃ የሚያስችለውን ሥልጠና በ‹‹Carpentry and Joinery›› ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆን መጋቢት 2014 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በ‹‹ On Site Building Construction Management›› ለደረጃ 4 ሊያበቃ የሚያስችለውን ሥልጠና ወስደው አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሮ ታየች ከጥር 25/2009-ነሐሴ 30/2010 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የጽዳት ሠራተኛ በመሆን እንዲሁም ከመስከረም 01/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በኩልፎ ካምፓስ ቤተ መጻሕፍት የሰርኩሌሽን ሠራተኛ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ወ/ሮ ታየች ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ታኅሣሥ 16/2016 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ወ/ሮ ታየች የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች እናት ነበሩ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ ታየች በለጠ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት