የኢትዮጵያ ሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር በየዓመቱ ብሩህ ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል  የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ያካሂዳል፡፡ በዚህ ውድድር አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ በማሸነፍ ከግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ ይሰለፋል፡፡ በተመሳሳይ በ2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የብሩህ ኢትዮጵያ  የቢዝነስ ሃሳብ ውድደር ተማሪዎችን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ሥልጠና በማሰልጠንና በማወዳደር የተሻለ ሃሳብ ያላቸውን ተማሪዎች ለብሩህ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የምንልክ መሆኑን እየገለፅን በዚህ ውድድርና ሥልጠና የነቃ ተሳትፎ እንድታደርጉ በአንክሮ እናሳስባለን፡፡ ምዝገባው የሚካሄደው  ከጥር 10 - 17/2016 ዓ.ም ሲሆን የቢዝነስ ሃሳብ ተወዳዳሪዎች በግል ወይም በቡድን መወዳደር ይችላሉ፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የመመዝገቢያ ሁኔታ በኦላይን ሲሆን፡-

ለመመዝገብ በዚህ ሊንክ https://forms.gle/uTdPkARHu4hxR1y28

ወደ ቴሌግራም ለመቀላቀል https://t.me/+fPM1qA6W62E3YjU0

 ማሳሰቢያ፡- ከመመዝገቢያ ሊንኩ በታች ባለው ሌላ ሊንክ ተጭነው ወደ ቴሌግራማችን መቀላቀላችሁን እንዳትረሱ፡፡ ሁሉም መረጃ
              በዚያ በኩል የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት