የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት የባህሪ ማሻሻያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከ “International Youth Fellowship” ጋር በመተባበር በአዕምሮ ውቅር (mindset) ዙሪያ ከኮሪያ በመጡ አሠልጣኞች ለጫሞ፣ ለዋናው ግቢ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ የዩኒቨርሲቲው መደበኛ፣ ኢ-መደበኛና ለሁሉም ሪሚዲያል ተማሪዎች፣ ለባይራ አዳሪ 2 ደ/ት/ቤት ተማሪዎች እና ለአርባ ምንጭ ከተማ መምህራን ከጥር 17-18/2016 ዓ.ም በዋናው ግቢ በሚገኝ አዳራሽ ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በዚህም መሠረት ሥልጠናው፡-

  • ለአርባ ምንጭ ከተማ መምህራን ጥር 17/2016 ዓ.ም ከ8፡00 ጀምሮ
  • ለጫሞና ዋናው ግቢ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ መደበኛ ተማሪዎች፣ ለመደበኛና ኢ-መደበኛ ሪሜዲያል ተማሪዎች እና ለባይራ አዳሪ 2 ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ጥር 18/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት