አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፌዴራል ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት/FDRE Construction Management Institute/ ጋር በመተባባር “Building Information Management/BIM”በሚል ርዕስ ለዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ እና ለውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች መምህራን፣ ለዩኒቨርሲቲው ግንባታ ፕሮጀክትና ለፋሲሊቲ አስተዳደር ዘርፍ ባለሙያዎች ከጥር 13 - 30/2016 ዓ.ም ድረስ ስለግንባታ ሞዴልንግ ቴክኖሎጂ ሥልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ሥልጠናው ‘’BIM - Architectural’’፣ ‘’BIM-structural”፣ “BIM-MEP-Mechanical’’፣ ‘’BIM-MEP Plumbing’’፣ “BIM-MEP-Electrical’’ እና “BIM-Project Management’’ በሚሉ ይዘቶች ይሰጣል፡፡ ዓላማውም የግንባታ ሥራዎች ወደ ተግባር ሲገቡ ልያጋጥሙ የሚችሉ የዲዛይን፣ የበርና መስኮት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ የሽንት ቤት እና ሌሎች ችግሮችን አስቀድሞ ለመከለከል የሚያስችል ክሂሎት ለማሳደግ የሚያግዝ ነው፡፡  ሞዴል ተሠርቶ በመተቸት ወደ ሥራ ለመግባት፣ ወደ ሥራ ከተገባ በኋላ የሚነሱ ትችቶችን ለመቀነስና ለድጋሚ ሥራ የሚወጣውን የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ወጪ ለማስቀረት የታለመ ሥልጠና ነው፡፡

ሥልጠናው ከጥር 13 - 30/2016 ዓ.ም ድረስ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት